zeno
Create a Station
Explore
Religious
Music
News
Podcasts
Bible
By Genre
By Location
By Language
Download App
Opens in a new window
Toggle Sidebar
zeno
DW | Amharic - News
Amharic
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Website
Episodes
Episodes
11
18 July 2026
ዳንጎቴ በምሥራቅ አፍሪቃ ለመጀመሪያው የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ፕሮጀክት ኬንያን ለምን መረጡ?
በቀን 700ሺህ በርሜል የተጣራ ነዳጅ ዘይት እንደሚያቀርብ የተነገረው ተቋሙ ኬንያን ብቻ ሳይሆን መላውን የምሥራቅ አፍሪቃ አካባቢ ይለውጣል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። ተቋሙ በአፍሪካ ሁለተኛው ትልቁ የነዳጅ ማጣሪያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በምስራቅ አፍሪቃ የነዳጅ አቅርቦትን፣ ንግድን እና የኢኮኖሚ እድገትን እንደገና ሊቀርጽ ይችላልም ተብሏል።
18 July 2026
ህወሓትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባ
ከሰላምና ለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ከበደ አሰፋ ህወሓት ላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና እንዲያደርግ ይህንን ሰልፍ መጥራታቸውን ገልፀዋል።
18 July 2026
«የምግብ ዕርዳታ ድጋፍ አልተደረገልንም»
"ርሀብ አለ በጣም፣ ሰው በጣም ተጎድቶ ነው ያለው። ህፃኖቹም ምንም ምንም ያገኙት ነገር የለም። ትልልቆቹም እየለመኑ ነው የሚበሉት፤ እኛም ዝም ብለን ነው ያለነው። "
18 July 2026
አፍሪካ የእንስሳት ሐብቷን በሚገባ መጠቀም እንዳልቻለች ተገለፀ
ዩጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ እየላከች ነው የሚባለውን የስጋ ምርት በተመለከተም፣ ያን ያህል የጎላ እንዳልሆና ምርቱን እያስገባ ያለውም አንድ ሆቴል መኾኑን ጠቅዋል።ምርቱ የተቀነባበረ ስለኾነም፣ እንደ ምግብነት በምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በኩል የገባ መኾኑን አስረድተዋል።
17 July 2026
የወጣቶች የፈጠራ ስራ እና ተቀባይነታቸው
በነቀምቴ ከተማ በፈጠራ ስራው ትልቅ ተቀባይነት ያገኘው ወጣት ሚካኤል መስፍን በ2007 ዓ.ም በሳይንስና ቴክኖሎጂ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል፡፡ በወቅቱ ሁለት ሰዎችን መሸከም የሚችል ሳይክል ከወዳደቁ ብረታ ብረቶች ሰርቶ ለሽልማት በቅቷል።በመቀጠል የብሎኬት ስራን የሚያዘመን ማሽኖችን በመስራት በከተማው ትልቅ ተቀባይነት አግኝተዋል፡
17 July 2026
በአሜሪካ ምርጫ ቻይና ጣልቃ ገብታለች ያሉት ትራምፕ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ቻይና በአሜሪካ ምርጫዎች ላይ ጣልቃ ገብታለች በሚል የቀረበውን ክስ በተመለከተ አዲስ ምርመራ እንዲደረግ አዘዙ። ትራምፕ ይህን ያሉት ትንንት ምሽት ለአሜሪካ ህዝብ ባደረጉት ንግግር ነዉ። የትራምፕ የስልጣናቸዉ አጋማሽ የምክር ቤት የሟሟያ ምርጫ ሊካሄድ የቀረዉ ሁለት ወራት ግድም ነዉ።
17 July 2026
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሰሜን ኢትዮጵያ ጉብኝቶች
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ሀገራቸው በትግራይ ክልል ለሰላም፣ ለመረጋጋት እና ለሰብአዊ ማገገም ያላትን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ መቀሌ መጓዛቸው ሲነገር፣ ጎንደር ላይ ደግሞ ስለ ሰላም ተስፋዎች እና ለኢትዮጵያ እና አሜሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ስለሚኖሩ ዕድሎች ስለመምከራቸው ተገልጿል።
17 July 2026
በትግራይ የሰላምና ለውጥ ም/ቤት በአዲስ አበባ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ
ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ምበትግራይ ክልል እየተፈጸመ ነው የተባለውን “የወጣቶች አፈሳ” የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ሊካሄድ ነዉ። አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በትግራይ ክልል “አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን” በሚል መርህ ለፌዴራል መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ ለማቅረብ የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡
12 July 2026
ሃገራዊ ምክክር የመጨረሻው ምዕራፍ ከተስፋ ባሻገር
ኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ለማድረግ ጥቂት ቀናት ቀርተዋታል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በምክክሩ ላይ ይሳተፋሉ የተባሉ ከአራት ሺ በላይ ተወያዮች አዲስ አበባ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ውጪ የምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ከሶስት ዓመታት በላይ እንደወሰደበት ታይቷል።
05 July 2026
እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ?
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።